መጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ፬ የሐዲስ ኪዳን መግቢያ

የሐዲስ ኪዳን መግቢያ

 

ሐዲስ ኪዳን

 

-        ኪዳን የሚለው ቃል ተካየደ ከሚለው ግስ የመጣ የግእዝ ቃል ነው፡፡ ‹‹ተካሄደ›› ማለት ተዋዋለ፣ ተስማማ፣ ተማማለ ማለት ሲሆን ኪዳን ማለትም ውል ፣ ስምምነት ፣ መሐላ ማለት ነው፡፡

-        ኪዳን በሁለት ወገኖች መካከል የሚመሠረት ውል ሲሆን ከተመሠረተ በኋላ በሁለቱ ወገኖች መካከል እንደ ሕግ ሆኖ የሚመሠረት ስምምነት ነው፡፡

-        በመጽሐፍ ቁጥስ ውስጥ ኪዳን ሲባል ከእግዚአብሔር ለሰዎች የተሰጠና ሰዎች በእምነት የተቀበሉት ውል ነው፡፡

-        ሐዲስ ኪዳን ከእግዚአብሔር ለሰዎች የተሰጠ የድኀነት ኪዳን ነው፡፡ ይኸውም በወልደ እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንሚያገኝ የሚያረጋግጥ ነው፡፡

-        የዚህ ድኅነት ኪዳን ቃላትም፡-

·       ያመነ የተጠመቀም ይድናል፣ /ማር16÷16/

·       በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው /ዮሐ 3÷36/

·       እውነት እውነት እላችኋላሁ በእኔ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው     /ዮሐ 6÷47/

·       ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃል በአፉም መስክሮ ይድናልና

     /ሮሜ 1ዐ÷1ዐ-13፣የሐዋ 2÷21/ የሚሉትና የመሳሰሉት ቃላት ናቸው፡፡

 

-        ሐዲስ ኪዳን ሲባል ፊተኛ ኪዳን እንዳለ ያመለክታል፡፡ 

ይህም ፊተኛ ኪዳን  ብሎይ ኪዳን ነው፡፡ ብሎይ ኪዳንን ‹‹ብሎይ›› ያሰኘው የሐዲስ ኪዳን መምጣት ነው፡፡

‹‹አዲስ ማለቱ ፊተኛውን አስረጅቷል›› እንዳለ /ዕብ 8÷13/

-        ሐዲስ የተባለውም፡-

1.      ካብ.ኪ. ያሳለፋቸው አንዳንድ ሥርዓቶች ስላሉ ነው፡፡

     ምሳሌ - ግዝረት /ቁላ.2÷11፣ ገላ 5÷6/

-        መሥዋዕት ኦሪት/ ዕብ 9÷9 እና 1ዐ/

2.     በልብ ጽላት ላይ መንፈስ የሚጻፍ አዲስ ውል ስለሆነ ነው

     /2ቆሮ.3÷3-6፣ ኤር. 31÷31-33፡፡/

-        ስለ ሐዲስ ኪዳን በብ.ኪ. የተነገረ ትንቢት በኤር.31÷31-34 ይገኛል፡፡ የዚህ ትንቢት ፍጻሜው ደግሞ በዕብ. 866-13 ላይ ይገኛል፡፡

-        የሐዲስ ኪዳን መሥራቹ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ የመሠረተውም በገዛ እራሱ ደም ሲሆን ጊዜውም በምሴተ ሐሙስ ነበር፡፡

ይህ የበሐዲስ ኪዳን. አመሠራረት በሚከተሉት ጥቅሶች ተመዝግቧል፡፡

     1/ ማቴ.26÷26-29፡፡                    3/ ሉቃ.22÷18-2ዐ

     2/ ማር.14÷22-25፡፡                    4/ 1ቆሮ.11÷23-25

ተመልከት፡፡

-        የሐዲስ ኪዳን ተስፋው የዘላለም ሕይወት ሲሆን ምልክቱም ቅ.ቁርባን ነው፡፡

ጥቅስ፡- ‹‹ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ኸይወት አለው አኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ፡፡›› /ዮሐ. 6÷54/

 

-        ሐዲስ ኪዳን የሚለው ይህ ስያሜ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስን ታሪክ እና ትምህርትን እንዲሁም ደቀመዛሙርቱ ሐዋርያት ስለ እርሱ ያስተማሩትን ሁሉ የያዘውን ሁለተኛውን የመጽሐፍ ቅዱስ ዐቢይ ክፍል ይመለከታል፡፡

 

-        በሐዲስ ኪዳን. ከክርስቶስ ልደት በኋላ ከ45-1ዐዐ ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ የቅዱሳት መጻሕፍት ስብስብ ነው፡፡

 

-        በሐዲስ ኪዳን. ጌታ እየሱስ ክርስቶስን በዓይናቸው ያዩትና ቃሉን በጆሮአቸው፣ በአጃቸው የሚሳሱት፣ ከእርሱ የተማሩትና በእርሱ የተመረጡት ደቀ መዛሙርት------   * ተከታዮች በመንፈስ ቅዱስ እየተመሩ የተጻፉት እውነተኛ መጽሐፍ ነው፡፡

 

-        በሐዲስ ኪዳን. በታሪክም ይሁን በትምህርት እንዲሁም በትንቢታዊ አቀራረብ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚገልጽ መጽሐፍ ነው፡፡

     ይህ ማለት የበሐዲስ ኪዳን. መጻሕፍት ማዕከላቸው ክርስቶስ ነው ማለት ነው፡፡

-        በሐዲስ ኪዳን. የብ.ኪ. ፍጻሜና አካል ስለሆነ በምሳሌና በትንቢት በብ.ኪ የተናገሩት ብዙዎች ቃላት በሐዲስ ኪዳን. ተጠቅሰው ፍጻሜአቸውና ትርጉማቸው ተገልጧል፡፡

የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት በተለያዩ ቅዱሳን ሰዎች በተለያዩ ቦታዎችና በተለያዩ ዘመናት የተጻፉ ሆነው ሳለ በአንድነት የተሰባሰቡትና ከሐሰተኞች መጻሕፍት ተለይተው የክርስቲያኖች የእምነት መመሪያ ሊሆኑ ይቻሉት በቤተክርስቲያን ቀኖና በተወሰነው መሠረት ነው፡፡

 

የሐዲስ ኪዳን ቀኖና 

 

- ቀኖና የሚለው ቃል መሠረቱ ‹‹ቃኔህ›› የሚለው የዕብራይስጥ ቃል ሲሆን በግሪከኛ ‹‹ካኖን›› ይባላል፡፡ ትርጉሙ መለኪያ ዘንግ፣ መቃ ማለት ነው፡፡ /ሕዝ. 4ዐ÷3፡፡ ራእይ 11÷1፡፡ ተመልከት/ ቀደም ሲል ቃሉ የአንድን ነገር እርዝማኔ ለመለካት የሚያገለግለውን መቃ፣ ወይም ዘንግ ያመለክት ነበር፡፡ በኋላ ግን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሁሉም ዘንድ ተቀባይነት ያላቸውን መንፈሳዊ ውሳኔዎችን /ድንጋጌዎችን/ ያመለክት ጀመር፡፡

 

- የሐዲስ ኪዳን ቀኖና ሲባልም በቤተክርስቲያን ደረጃ የተወሰኑትንና ተቀባይኀት ያላቸውን የበሐዲስ ኪዳን. መጻሕፍትን ቁጥርና ዝርዝር ያመለክታል፡፡

እነዚህም በቁጥርና በዝርዝር የተወሰኑት የበሐዲስ ኪዳን. መጻሕፍት የበሐዲስ ኪዳን. ቀኖናውያን መጻሕፍት ይባላሉ፡፡ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስና ሐዋርያት ያስተምሩባቸው የነበሩት ቀኖናውያን መጻሕፍት የብ.ኪ. መጻሕፍት ነበሩ፡፡ በኋላ ግን ሐዋርያት በመንፈስ ቅዱስ እየተመሩ የጻፉአቸው የበሐዲስ ኪዳን.መጻሕፍት ከብ.ኪ መጻሕፍት እኩል ቀኖናውያን ሆነዋል፡፡ ጸሐፊዎቹ መጻሕፍቱን ሲጽፉ በመንፈስ ቅዱስ እየተመሩ እንደሆነ ሁሉ የኋላ አባቶችም የበሐዲስ ኪዳን.መጻሕፍትን የሰበሰቡትና ቀኖናውያን መሆን የሚገባቸውን መርጠው ዝርዝራቸውንና ቁጥራቸውን የወሰኑት በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው ነው፣ ጌታችን መንፈስ ቅዱስን እንደሚልክ በተናገረበት ክፍል ‹‹… እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል›› ብሎ ቃሉ በገባው መሠረት አሁን ያለው የበሐዲስ ኪዳን. ቀኖና እንደሆነ እናምናለን፡፡ /ዮሐ.16÷12፡13፣ማቴ.28÷2ዐ/

 

የበሐዲስ ኪዳን.ቀኖና ለምን አስፈለገ?

ከሐዋርያት በኋላ እስከ 4ኛው ክ/ዘመን በነበረችው ቤተ ክርስቲያን የበሐዲስ ኪዳን. ቁጥርና ዝርዝር በማዕከላዊ ደረጃ በቀኖና አልተወሰነም ነበር፡፡ ስለሆነም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በአምልኮተ እግዚአብሔር ጊዜ መነበብ የሚገባቸውና ለክርስትና እምነት ትምህርት መመሪያና አስረጅ ሆነው መጠቀስ የሚችሉት የትኞቹ እንደሆኑ ለመለየት አስቸጋሪ ሆኖ ነበር፡፡ በመሆኑም ለዚህ ችግር መፍትሔ መስጠት አስፈለገ፡፡

 

  ስለዚህ የበሐዲስ ኪዳን. ቀኖና ያስፈለገበት ምክንያት፡-

 

1.      ሐራ ጥቃዎች /Heretics/ በሐዲስ ኪዳን. ጸሐፊዎች ስም ይጽፋቸው ከነበሩት ብዛት ካላቸው የውሸት መጻሕፍት በመንፈስ ቅዱስ የተጻፋትን እውነተኞቹን የበሐዲስ ኪዳን. መጻሕፍት ለመለየት ነው፡፡

 

2.     በየስፍራው የነበሩት አብያተ ክርስቲያናት የቤተ ክርስቲያን/ አባቶች እንዲሁም ሐራ ጥቃዎች በሐዲስ ኪዳን. መጻሕፍት ቁጥርና ዝርዝር ላይ የነበራቸውን የተለያየ አስተሳሰብ መርምሮ በማጣራት በዓለም ቤተ ክርስቲያን ሁሉ ተቀባይነት ያለውን የበሐዲስ ኪዳንዳንን ቁጥርና ዝርዝር በማዕከላዊ ደረጃ ለመወሰን ነው፡፡

 

የቀኖናው መመዘኛዎች፡-

 

      የበሐዲስ ኪዳን. መጻሕፍትን ከውሸት ጽሑፎችና በሌሎችም ምንባባዊት መጻሕፍት ለይቶ ለመምረጥና ለመሰብሰብ እንዲሁም ቀኖናውን ለመወሰን ቤተ ክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ እየተመራች የሚከተሉትን መመዘኛዎች ተጠቅማለች፡፡

 

1.       መጽሐፍ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን በዓይናቸው ያዩት ቃሉን በጆሮአቸው የሰሙት፣ ከእርሱ የተማሩት፣ ሐዋርያት ወይም የእነርሱ ረድአ /ጓደኛ/ የጻፈው መሆን አለበት፡፡

2.      መጽሐፍ ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስና ከሐዋርያት ጀምሮ ቀጥ ብሎ ከመጣው ትምህርተ ሃይማኖት የተለየ /የስህተት/ ትምህርት የሌለበት መሆን አለበት፡፡

 

3.      መጽሐፉ በመንፈስ ቅዱስ ስለ መጻፉ በአብዛኞቼ አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ የተመሰከረለትና ሙሉ ተቀባይነትን ያገኘ መሆን አለበት፡፡

 

    በሐዲስ ኪዳን. ማዕከላዊ ቀኖና አለመኖር ምክንያት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተፈጥረው የነበሩት ችግሮች በጣም ያሳሰባቸው የቤተ ክርስቲያን አባቶች በመንፈስ ቅዱስ ርዳታ እነዚህን መመዘኛዎች ተጠቅመው እውነተኛውን ቀኖና ወስነውልናል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ቅዱስ ያሬድ ማነው? ከዳንኤል ክብረት

መጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ፪