መጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ፪

የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊ


መጽሐፍ ቅዱስን የጻፉት ሰዎች ቅዱሳን ሰዎች ናቸው፡፡ነገር ግን ከራሳቸው አመንጭተው ሳይሆን በእግዚአብሔር ተልከው በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ጽፈውታል፡፡

ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር እስትንፋስ ነው፡፡ በውስጡ የያዛቸው ቅዱሣት መጻሕፍት ከአምላካችን ከእግዚአብሔር የተገኙ መጻሕፍት አምላካዊያት ይባላሉ፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሔር መንፈስ ስለመጻፉ የሚከተሉትን ጥቅሶች እንመለከታለን፡፡

1.      2ኛ ሳሙ 23፡2
2.     2ኛ ጢሞ 3፡16
3.     2ኛ ጴጥ 1፡2ዐ

በመንፈስ ቅዱስ ተመርተውና ተነድተው መጽሐፍ ቅዱስን የጻፉ ሰዎች ከተለያየ የሥራ መስክ የተጠሩ ናቸው፡፡ እንዲሁም በተለያየ ዘመን ነበር፡፡ ሆኖም የጻፉአቸውን መጻሕፍት ያስጻፉዋቸው አንድ የእግዚአብሔር መንፈስ ስለሆነ ቃሌም ሆነ መልዕክቱ ፈጽሞ አይጋጭም /አይጣላም/፡፡ ጸሐፊዎቹ በችሎታቸው በዕውቀታቸው የተለያዩ ሆነው ሳለ በእግዚአብሔር መንፈስ የጻፉአቸው ቅ/መጻሕፍት ግን ዋና ሐሳባቸው እና መልዕክታቸው አልተለያየም፡፡ በዚህም ምክንያት እኛ ለሕይወታችን መመሪያ መጽሐፍ ቅዱስን የበላይ አድርገን ተቀብለንዋል ይህም የመጽሐፍ ቅዱስ ሥልጣን ይባላል፡፡



የመጽሐፍ ቅዱስ ቀኖናዊነቱ

ቀኖና የሚለው ቃል ካኖን የሚለውን የግሪከኛ ቃል ሲሆን ትርጉሙም መለኪያ ዘንግ ማለት ነው፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ቀኖና ስንልም መጽሐፍ የያዘውን የመጻሕፍት ቁጥር/ብዛት/ ያመለክታል፡፡ እንደሚታወቀው መጽሐፍ ቅዱስ የብሉኪዳንና የአዲስ ኪዳንን መጻሕፍት የያዘ ሲሆን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ.ክ.ቀኖና መሠረት ብ.ኪዳን 46 አ.ኪዳን ዳግም 35 በድምሩ 81 መጻሕፍትን ትቀበላለች… /ፍት.ነ.አንቀጽ 2 ርእሱን ተመ./ የመጻሕፍቱን ቁጥር በቀኖና ቁጥር በቀኖና መወሰን ያስፈለገበት ምክንያት፡-

1.      በእግዚአብሔር መንፈስ በነበያትና በሐዋርያት አማካኝነት የተጻፉትን ቅዱሳት መጻሕፍትን ከሌሎች መጻሕፍት ለመለየት፡
2.     በቅዱሳን ጸሐፊዎች ስም ይጻፉ ከነበሩት የስህተት ጽሑፎች እስትንፋስ እግዚአብሔር የሆኑትን መጻሕፍት ለይቶ ለመቀበል፡፡
3.     ለቤተክርስቲያን እምነትና ትምህርት መሠረት /አብነት/ የሚሆን የተወሰነ ቅዱስ መጽሐፍ እንዲኖራት ለማድረግ ነው፡፡

በዚህ መሠረት በተለያዩ ጊዜያት የተጻፉት የበ.ኪ. እና የአ.ኪ.መጻሕፍት በኋላ በተነሡት ሊቃውንት /የእግዚአብሔር ሰዎች/ አማካኝነት የቀኖናው ቁጥር ተወስዷል፡፡ 

ተብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ቁጥር /ቀኖና/ የተወሰደው በሰባ ሊቃናት አማካኝነት በ285 ቅ.ል.ክ. ሲሆን የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ደግሞ በካርቴጂ ጉባዔ በ397 ዓ.ም ነው፡፡ ከዚህ ቀጥሎ 81 ዱን መጻሕፍት በዝርዝር እናቀርባለን፡፡

የ81ዱ ቅ/መጻሕፍት ዝርዝር
 ሀ. የብ.ኪ.መጻሕፍት
1.
ኦሪት ዘፍጥረት
24.
መጽሐፈ ምሳሌ ዘሰለሞን
2.
 ››   ዘጸአት
25.
  ››   ተግሣጽ
3
 ››   ዘሌዋዊያን
26.
  ››   ጥበቡ
4.                    
 ››   ዘኅልቁ
27.
  ››   መክብብ
5.
 ››   ዘዳግም
28.
መኃለየ መኃለየ ዘሰለሞን
6.
መጽሐፈ ኢያሱ ወልደነዌ
29.
ትንቢተ ኢሳያስ
7.
 ››   መሳፍንት
3ዐ.
  ››   ኤርሚያስ
8.
 ››  ሩት
31.
  ››   ሕዝቅኤል
9.
 ››  ዮዲት
32.
  ››   ዳንኤል
1ዐ.
 ››  1ኛ ሳሙኤል
33.
  ››   ሆሴዕ
11.
 ››  ሳሙኤል ካልአ
34.
  ››   አሞጽ
12.
 ››  ሳሙኤል ቀዳማዊ
35.
  ››   ሚኪያስ
13.
 ››  ነግሥት ካልአ
36.
  ››   ኢዮኤል
14.
 ››  ዜና መዋዕለ ቀዳሚ
37.
  ››   አብድዬ
15.
 ››  ዜና መዋዕል ካልእ
38.
  ››   ዮናስ
16.
 ››  ዕዝራ ጸሐፊ ቀዳማዊ
39.
  ››   ናሆም
17.
 ››  ዕዝራ ጸሐፊ ካልእ
4ዐ.
  ››   ዕንባቆም
18.
 ››  አስቴር
41.
  ››   ሶፎንያስ
















ለ. የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት

1.
የማቴዎስ ወንጌል
19.
ወደ ዕብራውያን
2.
የማርቆስ ወንጌል
20.
የጴጥሮስ መልእክት 1ኛ
3.
የሉቃስ ወንጌል
21.
የጴጥሮስ መልእክት 2ኛ
4.
የዩሐንስ ወንጌል
22.
የዩሐንስ መልእክት 1ኛ
5.
የሐዋርያት ሥራ
23.
የዩሐንስ መልእክት 2ኛ
6.
ወደ ሮሜ ሰዎች
24.
የዩሐንስ መልእክት 3ኛ
7.
ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1ኛ
25
የያቆብ መልእክት
8.
ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2ኛ
26.
የይሁዳ መልእክት
9.
ወደ ገላትያ ሰዎች
27.
የዩሐንስ ራእይ
1ዐ.
ወደ ኤፌሶን ሰዎች
28.
ትእዛዝ ሲኖዶስ
11.
ወደ ፌልጵስዩስ ሰዎች
29.
ግጽው ሲኖዶስ
12.
ወደ ቆላስደስ ሰዎች
30.
አብጥሊስ ሲኖዶስ
13.
ወደ ተሰሌንቄ  ሰዎች 1ኛ
31.
ሥርዓተ ድጓ ሲኖዶስ
14.
ወደ ተሰሌንቄ ሰዎች 2ኛ
32.
1ኛ መጽሐፍ ኪዳን
15.
ወደ ጢሞቴዎስ 1ኛ
33.
2ኛ መጽሐፍ ኪዳን
16.
ወደ ጢሞቴዎስ 2ኛ
34.
መጽሐፈ ቀሌምንጦስ
17
ወደ ቲቶ
35.
ዲድስቅልያ

                               ምንጭ  ፡- ‹‹አጭር የታሪክ፣ የሃይማኖት የሥርዓት መጽሐፍ›› በ1975 ዓ.ም ከቅዱስ  ሲኖዶስ የተዘጋጀ

ገጽ 68-71 

Comments

Popular posts from this blog

ቅዱስ ያሬድ ማነው? ከዳንኤል ክብረት

መጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ፬ የሐዲስ ኪዳን መግቢያ