Posts

Showing posts from July, 2018

መጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ፫

Image
የመጽሐፍ ቅዱስ አከፋፈል፡- መጽሐፍ ቅዱስ ባጠቃላይ በሁለት ታላላቅ ክፍሎች ይከፈላል 1.       ብሉይ ኪዳን፡- ከክርስቶስ ልደት በፊት የተጻፉ መጻሕፍት ናቸው በአብዛኛው የተፃፉት በነበያት ነው፡፡ 2.      አዲስ ኪዳን፡- ከክርስቶስ ልደት በኋላ በሐዋርያት የተጻፉ መጻሕፍት ናቸው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ከያዘው ቃል አንፃር በዘመናት ሲታይ በሦስት ይከፈላል፡፡ 1.       ዘመነ አበው፡- በኦሪት ዘፍጥረት የተገለጠው ነው፡፡ 2.      ዘመነ ኦሪት ፡- ከኦሪት ዘጸአት እስከ ትንቢተ ሚልክያስ ድረስ ድረስ የተገለጠው ነው፡፡ 3.      ዘመነ ክርስትና /ወንጌል/፡- በአዲስ ኪዳን መጻሕፍት የተመዘገበው ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት ለመጥቀስ አመቺ እንዲሆን በውስጡ የያዛቸው ቅ/መጻሕፍት እያንዳንዳቸው በምዕራፍና በቁጥር ተከፍለዋል፡፡ ከጥንት ጀምሮ ቅዱሳት መጻሕፍተን የሚገለብጡ ሰዎች ምዕራፍና ቁጥር ለማውጣት ሞክረዋል፡፡ ነገር ግን እንደገና አሁን ባለው መልኩ የተከፈለው እንደሚከተለው ይሆናል፡፡ 1.       በምዕራፍ የተከፈለው በ1228 ዓ.ም ሲሆን የካንተርበሪ ሊቀ ጳጳስ በነበረው በስቴፈን ላንግተን አማካይነት ነው፡፡ 2.      ምዕራፍ በቁጥር የተከፈለው ደግሞ በ1551 ዓ.ም ሲሆን ሮበርት ናታን (ስቴፋነስ) በተባለው የፈረንሳይ ሰው አማካይነት ነው፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በምዕራፍና በቁጥር ለመጥቀስ ሲያስፈልግ ሥርዓተ ነጥቦችንና የምህፃረ ቃላት ምልክቶችን /መሪ ምልክቶችን/ በተመለከተ፣ እንዲሁም ስለ ጥቅሶች ቁርኝት የተሰጠውን መግለጫ ማጥናት ያስፈልጋል፡፡ ይኸውም መግለጫ የሚገኘው በመጽሐፍ ቅዱስ መካከል በአ.ኪ. መግቢያ የመጀመሪያ ቅጠል ነው፡፡