Posts

መጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ፬ የሐዲስ ኪዳን መግቢያ

Image
የሐዲስ ኪዳን መግቢያ   ሐዲስ ኪዳን   -         ኪዳን የሚለው ቃል ተካየደ ከሚለው ግስ የመጣ የግእዝ ቃል ነው፡፡ ‹‹ ተካሄደ ›› ማለት ተዋዋለ፣ ተስማማ፣ ተማማለ ማለት ሲሆን ኪዳን ማለትም ውል ፣ ስምምነት ፣ መሐላ ማለት ነው፡፡ -         ኪዳን በሁለት ወገኖች መካከል የሚመሠረት ውል ሲሆን ከተመሠረተ በኋላ በሁለቱ ወገኖች መካከል እንደ ሕግ ሆኖ የሚመሠረት ስምምነት ነው፡፡ -         በመጽሐፍ ቁጥስ ውስጥ ኪዳን ሲባል ከእግዚአብሔር ለሰዎች የተሰጠና ሰዎች በእምነት የተቀበሉት ውል ነው፡፡ -         ሐዲስ ኪዳን ከእግዚአብሔር ለሰዎች የተሰጠ የድኀነት ኪዳን ነው፡፡ ይኸውም በወልደ እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንሚያገኝ የሚያረጋግጥ ነው፡፡ -         የዚህ ድኅነት ኪዳን ቃላትም፡- ·        ያመነ የተጠመቀም ይድናል፣ /ማር16÷16/ ·        በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው /ዮሐ 3÷36/ ·        እውነት እውነት እላችኋላሁ በእኔ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው     /ዮሐ 6÷47/ ·        ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃል በአፉም መስክሮ ይድናልና      /ሮሜ 1ዐ÷1ዐ-13፣የሐዋ 2÷21/ የሚሉትና የመሳሰሉት ቃላት ናቸው፡፡   -         ሐዲስ ኪዳን ሲባል ፊተኛ ኪዳን እንዳለ ያመለክታል፡፡  ይህም ፊተኛ ኪዳን  ብሎይ ኪዳን ነው፡፡ ብሎይ ኪዳንን ‹‹ ብሎይ ›› ያሰኘው የሐዲስ ኪዳን መምጣት ነው፡፡ ‹‹ አዲስ ማለቱ ፊተኛውን አስረጅቷል ›› እንዳለ /ዕብ 8÷13/ -         ሐዲስ የተባለውም፡- 1.       ካብ.ኪ. ያሳለፋቸው አንዳንድ ሥርዓቶች ስላሉ ነው፡፡      ምሳሌ - ግ

መጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ፫

Image
የመጽሐፍ ቅዱስ አከፋፈል፡- መጽሐፍ ቅዱስ ባጠቃላይ በሁለት ታላላቅ ክፍሎች ይከፈላል 1.       ብሉይ ኪዳን፡- ከክርስቶስ ልደት በፊት የተጻፉ መጻሕፍት ናቸው በአብዛኛው የተፃፉት በነበያት ነው፡፡ 2.      አዲስ ኪዳን፡- ከክርስቶስ ልደት በኋላ በሐዋርያት የተጻፉ መጻሕፍት ናቸው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ከያዘው ቃል አንፃር በዘመናት ሲታይ በሦስት ይከፈላል፡፡ 1.       ዘመነ አበው፡- በኦሪት ዘፍጥረት የተገለጠው ነው፡፡ 2.      ዘመነ ኦሪት ፡- ከኦሪት ዘጸአት እስከ ትንቢተ ሚልክያስ ድረስ ድረስ የተገለጠው ነው፡፡ 3.      ዘመነ ክርስትና /ወንጌል/፡- በአዲስ ኪዳን መጻሕፍት የተመዘገበው ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት ለመጥቀስ አመቺ እንዲሆን በውስጡ የያዛቸው ቅ/መጻሕፍት እያንዳንዳቸው በምዕራፍና በቁጥር ተከፍለዋል፡፡ ከጥንት ጀምሮ ቅዱሳት መጻሕፍተን የሚገለብጡ ሰዎች ምዕራፍና ቁጥር ለማውጣት ሞክረዋል፡፡ ነገር ግን እንደገና አሁን ባለው መልኩ የተከፈለው እንደሚከተለው ይሆናል፡፡ 1.       በምዕራፍ የተከፈለው በ1228 ዓ.ም ሲሆን የካንተርበሪ ሊቀ ጳጳስ በነበረው በስቴፈን ላንግተን አማካይነት ነው፡፡ 2.      ምዕራፍ በቁጥር የተከፈለው ደግሞ በ1551 ዓ.ም ሲሆን ሮበርት ናታን (ስቴፋነስ) በተባለው የፈረንሳይ ሰው አማካይነት ነው፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በምዕራፍና በቁጥር ለመጥቀስ ሲያስፈልግ ሥርዓተ ነጥቦችንና የምህፃረ ቃላት ምልክቶችን /መሪ ምልክቶችን/ በተመለከተ፣ እንዲሁም ስለ ጥቅሶች ቁርኝት የተሰጠውን መግለጫ ማጥናት ያስፈልጋል፡፡ ይኸውም መግለጫ የሚገኘው በመጽሐፍ ቅዱስ መካከል በአ.ኪ. መግቢያ የመጀመሪያ ቅጠል ነው፡፡

መንፈሳዊ ትዳር

Image

Muaze Tibrbat D/n Daniel Kibret

መጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ፪

Image
የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊ መጽሐፍ ቅዱስን የጻፉት ሰዎች ቅዱሳን ሰዎች ናቸው፡፡ነገር ግን ከራሳቸው አመንጭተው ሳይሆን በእግዚአብሔር ተልከው በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ጽፈውታል፡፡ ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር እስትንፋስ ነው፡፡ በውስጡ የያዛቸው ቅዱሣት መጻሕፍት ከአምላካችን ከእግዚአብሔር የተገኙ መጻሕፍት አምላካዊያት ይባላሉ ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሔር መንፈስ ስለመጻፉ የሚከተሉትን ጥቅሶች እንመለከታለን፡፡ 1.       2ኛ ሳሙ 23፡2 2.      2ኛ ጢሞ 3፡16 3.      2ኛ ጴጥ 1፡2ዐ በመንፈስ ቅዱስ ተመርተውና ተነድተው መጽሐፍ ቅዱስን የጻፉ ሰዎች ከተለያየ የሥራ መስክ የተጠሩ ናቸው፡፡ እንዲሁም በተለያየ ዘመን ነበር፡፡ ሆኖም የጻፉአቸውን መጻሕፍት ያስጻፉዋቸው አንድ የእግዚአብሔር መንፈስ ስለሆነ ቃሌም ሆነ መልዕክቱ ፈጽሞ አይጋጭም /አይጣላም/፡፡ ጸሐፊዎቹ በችሎታቸው በዕውቀታቸው የተለያዩ ሆነው ሳለ በእግዚአብሔር መንፈስ የጻፉአቸው ቅ/መጻሕፍት ግን ዋና ሐሳባቸው እና መልዕክታቸው አልተለያየም፡፡ በዚህም ምክንያት እኛ ለሕይወታችን መመሪያ መጽሐፍ ቅዱስን የበላይ አድርገን ተቀብለንዋል ይህም የመጽሐፍ ቅዱስ ሥልጣን ይባላል፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ቀኖናዊነቱ ቀኖና የሚለው ቃል ካኖን የሚለውን የግሪከኛ ቃል ሲሆን ትርጉሙም መለኪያ ዘንግ ማለት ነው፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ቀኖና ስንልም መጽሐፍ የያዘውን የመጻሕፍት ቁጥር/ብዛት/ ያመለክታል፡፡ እንደሚታወቀው መጽሐፍ ቅዱስ የብሉኪዳንና የአዲስ ኪዳንን መጻሕፍት የያዘ ሲሆን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ.ክ.ቀኖና መሠረት ብ.ኪዳን 46 አ.ኪዳን ዳግም 35 በድምሩ 81 መጻሕፍትን ትቀበላለች… /ፍት.ነ.አንቀጽ 2 ርእሱን ተመ./ የመጻሕፍቱን ቁ